Thursday 14 January 2016

**ያምላክ ስም አለበት**


ቀድሞ ያሰበውን በልቡ ተመኝቶ፤
ቢሰጠው ፈጣሪ የውስጡን አይቶ፤
የበኩር ልጁን ሚካኤል ሊለው፤
በልቡ፣በውስጡ ቃል-ኪዳን ነበረው፤
ምኞት ተሳካና ኦላም ፈቀደና፤
ወንድ ልጅ ከነ-ቃጭሉ............
ሚካኤል ተባለ ምስጋናንም በስሙ!
የግዕዙ ትርጓሜ በረከት ያዘለ፤
እንደ እግዚአብሔር ያለ፤ማንም የለም ተባለ
....የልብ ሲሞላ ሲሳካም ምኞት፤
ፀሎት ሲሰማ ሲደርስ ከፀባዎት፤
ይቀርብ የለም ወይ ምስጋና በእውነት?፤
የሚካኤል ስሙም ህያው ነው በረከት፤
ያምላክ ስም አለበት።
 
✍✍ #ታታ_አፍሮ +Tata Afro 

‹‹....በመጀመሪያ ወንድ ልጅን ከወልድኩ ሚካኤል ነው የምለው......›› +Teddy Afro 
 
 
 
 
 


1 comment:

  1. ያምላክ ስም አለበት ፡ ቃላት ሲሰባጠር ቴዲ አፍሮ

    ReplyDelete