Tuesday, 29 December 2015
Friday, 11 December 2015
Wednesday, 9 December 2015
Sunday, 6 December 2015
<ኢትዮጵያ(ኢትዮጵያዊነት)ገዥ ፍቅር ማለት ነው> ኢትዮጵያዊነት ወደ ትክክለኛ አቅሙ የሚመለሰው ሙሉ ፍቅር ሲሆን ነው! ሙሉ ፍቅር ውሸት አይደለም ፍቅር ላለመሆን እሚያስችሉ በቂ የሆኑ የማንደሰትባቸው እና ጥሩ እንዳናስብ የሚያደርጉን በቂ ምክንያቶች በዚ አለም ብዙ ናቸው ነገር ግን እኛ ሙሉ ለመሆን ከፈለግን ከቀደመው ነገር ጥሩ የሆነውን ነገር ወስደን ጥሩ ያልሆነውን ነገር እንዳይደገም አርገን ካሰብን የማንዋደድበት የማንከባበርበት የማንተባበርበት ምንም ምክንያት የለም! የዛን ጊዜ ሙሉ ኢትዮጵያ የሚለውን አቅም እናገኛለን ያ ሙሉ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ገዥ ፍቅር ነው። "ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን"
"በርበሬው አጨሰኝ"
"በሳልሳዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን"
ያግድም አግድም ሄጄ ብዙ ተመክሬ
አልሰማም ሰላልኩኝ
በእናቴ ምድጃ ቁልቁል ተደፍቼ በርበሬ
ታጠንኩኝ
በአይኖቼ እያነባሁ ባፌ እያስነጠስኩኝ
እንደምንም ብዬ እናቴን በመሀል እንዲህ
ስል ጠየኩኝ
አባዬ ልጅ ሳይሆን በድሜ እየበለጠን
ምን አጥፍቶ ይሁን ሲጋራ የሚታጠን
ብዬ ብጠይቃት ፀጉሬን ጨምድዳ ደፍቃኝ ወደ ጭሱ
ዝም ብለህ ታጠን ለየት ይላል የሱ
ከህሊናው አለም ሲጣላ ከራሱ
ገላጋይ አቶ ነው ባፍና ባፍንጫው የሚወጣው ጭሱ
እናትና አባቱ እንዳንተ በጊዜ ቢያጥኑት በበርበሬ
ብርቅ አይሆንም ነበር ለትንባሆ ዛሬ
ዛሬም ያንተን ጥጋብ ልክ ካላገባው
የበርበሬ ጭሱ
ትንሽ ከፍ ስትል ትብሳለህ ከሱ
ቶሎ ካልተዘጋ የአመል በራፍህ
ይገባል ሲጋራ በመሀል ጣትህ
አለችና እናቴ ደግማ ወደጭሱ አንዴ
ብትመልሰኝ
የወደፊቱን ሱስ ነቅሎ እያስነጠሰኝ
ሲጋራ እንዳላጨስ በርበሬው አጨሰኝ
"በሳልሳዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን"
ያግድም አግድም ሄጄ ብዙ ተመክሬ
አልሰማም ሰላልኩኝ
በእናቴ ምድጃ ቁልቁል ተደፍቼ በርበሬ
ታጠንኩኝ
በአይኖቼ እያነባሁ ባፌ እያስነጠስኩኝ
እንደምንም ብዬ እናቴን በመሀል እንዲህ
ስል ጠየኩኝ
አባዬ ልጅ ሳይሆን በድሜ እየበለጠን
ምን አጥፍቶ ይሁን ሲጋራ የሚታጠን
ብዬ ብጠይቃት ፀጉሬን ጨምድዳ ደፍቃኝ ወደ ጭሱ
ዝም ብለህ ታጠን ለየት ይላል የሱ
ከህሊናው አለም ሲጣላ ከራሱ
ገላጋይ አቶ ነው ባፍና ባፍንጫው የሚወጣው ጭሱ
እናትና አባቱ እንዳንተ በጊዜ ቢያጥኑት በበርበሬ
ብርቅ አይሆንም ነበር ለትንባሆ ዛሬ
ዛሬም ያንተን ጥጋብ ልክ ካላገባው
የበርበሬ ጭሱ
ትንሽ ከፍ ስትል ትብሳለህ ከሱ
ቶሎ ካልተዘጋ የአመል በራፍህ
ይገባል ሲጋራ በመሀል ጣትህ
አለችና እናቴ ደግማ ወደጭሱ አንዴ
ብትመልሰኝ
የወደፊቱን ሱስ ነቅሎ እያስነጠሰኝ
ሲጋራ እንዳላጨስ በርበሬው አጨሰኝ
*ግርማዊነቶ* Teddy Afro
አልሄድ አልሄድ አልሄድ እያለኝ
ልቤ እየተነሳ አሃ ልቤ እየተነሳ
ምሎ ምሎ ምሎ ሲገዘት
በይሁድ አንበሳ አሃ በይሁድ አንበሳ
አጋር ቢሉህ አጋዥ ስዩመ እግዚአብሔር ዘእምነገዳ
ንጉስ ቀዳማዊ አሃ ንጉስ ቀዳማዊ
አለኝ አለኝ ታሪካቸው ኑር ባገር
ሆነን አፍሪካዊ አሃ ሆነን አፍሪካዊ
ጁዳ አንበሳ..አራት ኪሎ
ቢከቱትም...ስድስት ኪሎ
ጥላ ሆነ...ትልቅ ዋርካ
ላንድነቷ.....ለአፍሪካ
አራዳ ታቦቱ በፒያሳ
ቀዳማዊ ንጉስ ጁዳ አንበሳ
ቀዳማዊ ጁዳ አንበሳ
/ግርማዊነቶ ግርማዊነቶ የት እንደራሴ
የአፍሪካ አባት ሀይለ ስላሴ(×2)/X2
አዝማች..
ጀሞ ጀሞ ጀሞ ኬንያታ ካኒጎርማ
መክረው ከግርማዊ አሃ መክረው ከግርማዊ
አርበኛ የጥቁር ሞጋች በአፍሪካ ተወካይ
ሆኑ ቀዳማዊ አሃ ሆኑ ቀዳማዊ
አብሮ የመኖር ክቡር የሚፈታው ታላቅ
ህልም የነበራቸው አሃ ህልም የነበራቸው
አጋር ቢሉህ አጋዥ ስዩመ እግዚአብሔር ዘእምነገዳ
ግርማዊነታቸው አሃ ግርማዊነታቸው
ጁዳ አንበሳ..አራት ኪሎ
ቢከቱትም...ስድስት ኪሎ
ጥላ ሆነ...ትልቅ ዋርካ
ላንድነቷ.....ለአፍሪካ
እነ ጀሞ.... ኬኒያታ
የኖራቸው... ትልቅ ቦታ
ከተፈሪ ...መክረው ለካ
ተሞከረ ....ፓን አፍሪካ
አራዳ ታቦቱ በፒያሳ
ቀዳማዊ ንጉስ ጁዳ አንበሳ
ቀዳማዊ ንጉስ ጁዳ
/ግርማዊነቶ ግርማዊነቶ የት እንደራሴ
የአፍሪካ አባት ሀይለ ስላሴ(×2)/X2
Saturday, 5 December 2015
*ግርማዊነቶ* Teddy Afro
አልሄድ አልሄድ አልሄድ እያለኝልቤ እየተነሳ አሃ ልቤ እየተነሳ
ምሎ ምሎ ምሎ እስኪጋፈጥ
የይሁድ አንበሳ አሃ የይሁድ አንበሳ
አጋር ቢሉህ አጋዥ ስዩመ እግዚአብሔር ዘእምነገዳ
ንጉስ ቀዳማዊ አሃ ንጉስ ቀዳማዊ
አለኝ አለኝ ታሪካቸው እንኑር ባገር
ሆነን አፍሪካዊ አሃ ሆነን አፍሪካዊ
ጁዳ አንበሳ...አራት ኪሎ
ቢከቱትም...ስድስት ኪሎ
ጥላ ሆነ... ትልቅ ዋርካ
ለአንድነቷ.....ለአፍሪካ
አራዳ ታቦቱ በፒያሳ
ቀዳማዊ ንጉስ ጁዳ አንበሳ(×2)
ግርማዊነቶ የእንደራሴ የአፍሪካ አባት ሀይለ ስላሴ(×2)
አዝማች..
ጀሞ ጀሞ ጀሞ ኬንያታ ካኒጎርማ
መክረው ከግርማዊ አሃ መክረው ከግርማዊ
በእኛ የጥቁር ሞጋች በአፍሪካ ተወካይ
ሆኑ ቀዳማዊ አሃ ሆኑ ቀዳማዊ
አብሮ የመኖር ክቡር የሚፈታው ታላቅ
ህልም የነበራቸው አሃ ህልም የነበራቸው
አጋር ቢሉህ አጋዥ ስዩመ እግዚአብሔር ዘእምነገዳ
ግርማዊነታቸው አሃ ግርማዊነታቸው
ጁዳ አንበሳ..አራት ኪሎ
ቢከቱትም...ስድስት ኪሎ
ጥላ ሆነ...ትልቅ ዋርካ
ላንድነቷ.....ለአፍሪካ
እንዴት ሆነው... ኬንያታ
የኖራቸው.... ትልቅ ቦታ
ከተፈሪ ...መክረው ለካ
ተሞከረ ....ፓን አፍሪካ
አራዳ ታቦቱ በፒያሳ
ቀዳማዊ ንጉስ ጁዳ አንበሳ(×2)
ግርማዊነቶ የእንደራሴ
የአፍሪካ አባት ሀይለ ስላሴ(×2)
**ባልደራሱ** Teddy Afro
ከቀን ባራተኛው በዕለተ ሐሙስ
ከወንድሜጋር ስንጋልብ ፈረስ
አልያዘውም ኖሮ ልጓሙን አጥብቆ
አለፈች ህይወቱ ከፈረስ ላይ ወድቆ
እየጠበቀችን እምዬ ከቤት
እንዴት ላረዳት ነው የወንድሜን ሞት
ባልደራሱ........ አልተገራም ወይ ፈረሱ/X2
ባ....ልደራሱ
ምንብዬ ልንገራትX4
ምንብዬ?
ምንብዬ ልንገራትX4
ለምዬ ምንብዬ
ልንገራትX4
ምንብዬ?
ምንብዬ ልንገራትX4
ለምዬ!
ባ........ ባልደራሱ? አልተገራም ወይ ፈረሱ
አልተገራም ወይ ወይ.....?
አልተገራም ወይ ወይ.....?
አንተ ባልደራስ የፈረስ አባት
ነፍሱን ከገነት ለማታስገባት
ወይኔ ወይኔ
ለናቴ ልጅ ወይኔ! ወይኔ!
ከሜዳው ነው ወይ ወይ ከፈረሱ
ለሞት ያበቃው ምንድነው እሱ?
ወይኔ ወይኔ
ለናቴ ልጅ ወይኔ! ወይኔ!
ሳታበጃጀው ሉጋም ግላሱን
አንድ የናቴን ልጅ ነሳኸው ነፍሱን
ወይኔ ወይኔ
ለናቴ ልጅ ወይኔ! ወይኔ!
Friday, 4 December 2015
**ሞቶ ማሸነፍ**
በሳልሳዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን
ፈሪ ሸሽቶ ሲድን ባፉ ሊሾምበት
ሺ ገዳይ ነኝ ይላል ሺ ሟች በሌለበት
በየ ጦሩ ሜዳ በየትግሉ አቀበት
ጀግናው ሞቶ አልቆ ማን ይመስክርበት
የኋሊት ተሂዶም ፋኖ በዋለበት
ሬሳ ቢቆጠር
የሞተ ካለ እንጂ በቃላቱ ጠጠር
አንድም ሰው ላይገኝ የሱ ጦር የወጋው
አላዩም ብሎ ነው ለቀሪ ሚያወጋው
እኛም ሁልጊዜ የተረፈ አግንነን
የሞተ እየረሳን
ፈሪ በምላሱ ሰላም ከሚነሳን
ገዳይ ብቻ ማድነቅ እንዳይሆንብን ሱስ
ሞቶ ማሸነፍን እንማር ከ እየሱስ!
Subscribe to:
Posts (Atom)