Friday, 4 December 2015



**ሞቶ ማሸነፍ**
በሳልሳዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን

ፈሪ ሸሽቶ ሲድን ባፉ ሊሾምበት
ሺ ገዳይ ነኝ ይላል ሺ ሟች በሌለበት
በየ ጦሩ ሜዳ በየትግሉ አቀበት
ጀግናው ሞቶ አልቆ ማን ይመስክርበት
የኋሊት ተሂዶም ፋኖ በዋለበት
ሬሳ ቢቆጠር
የሞተ ካለ እንጂ በቃላቱ ጠጠር
አንድም ሰው ላይገኝ የሱ ጦር የወጋው
አላዩም ብሎ ነው ለቀሪ ሚያወጋው
እኛም ሁልጊዜ የተረፈ አግንነን
የሞተ እየረሳን
ፈሪ በምላሱ ሰላም ከሚነሳን
ገዳይ ብቻ ማድነቅ እንዳይሆንብን ሱስ
ሞቶ ማሸነፍን እንማር ከ እየሱስ!

1 comment: