**ባልደራሱ** Teddy Afro
ከቀን ባራተኛው በዕለተ ሐሙስ
ከወንድሜጋር ስንጋልብ ፈረስ
አልያዘውም ኖሮ ልጓሙን አጥብቆ
አለፈች ህይወቱ ከፈረስ ላይ ወድቆ
እየጠበቀችን እምዬ ከቤት
እንዴት ላረዳት ነው የወንድሜን ሞት
ባልደራሱ........ አልተገራም ወይ ፈረሱ/X2
ባ....ልደራሱ
ምንብዬ ልንገራትX4
ምንብዬ?
ምንብዬ ልንገራትX4
ለምዬ ምንብዬ
ልንገራትX4
ምንብዬ?
ምንብዬ ልንገራትX4
ለምዬ!
ባ........ ባልደራሱ? አልተገራም ወይ ፈረሱ
አልተገራም ወይ ወይ.....?
አልተገራም ወይ ወይ.....?
አንተ ባልደራስ የፈረስ አባት
ነፍሱን ከገነት ለማታስገባት
ወይኔ ወይኔ
ለናቴ ልጅ ወይኔ! ወይኔ!
ከሜዳው ነው ወይ ወይ ከፈረሱ
ለሞት ያበቃው ምንድነው እሱ?
ወይኔ ወይኔ
ለናቴ ልጅ ወይኔ! ወይኔ!
ሳታበጃጀው ሉጋም ግላሱን
አንድ የናቴን ልጅ ነሳኸው ነፍሱን
ወይኔ ወይኔ
ለናቴ ልጅ ወይኔ! ወይኔ!
No comments:
Post a Comment