Sunday, 6 December 2015

      "በርበሬው አጨሰኝ"
"በሳልሳዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን"

ያግድም አግድም ሄጄ ብዙ ተመክሬ
  አልሰማም ሰላልኩኝ
በእናቴ ምድጃ ቁልቁል ተደፍቼ በርበሬ
    ታጠንኩኝ
በአይኖቼ እያነባሁ ባፌ እያስነጠስኩኝ
እንደምንም ብዬ እናቴን በመሀል እንዲህ
      ስል ጠየኩኝ
አባዬ ልጅ ሳይሆን በድሜ እየበለጠን
ምን አጥፍቶ ይሁን ሲጋራ የሚታጠን
ብዬ ብጠይቃት ፀጉሬን ጨምድዳ ደፍቃኝ ወደ ጭሱ
ዝም ብለህ ታጠን ለየት ይላል የሱ
ከህሊናው አለም ሲጣላ ከራሱ
ገላጋይ አቶ ነው ባፍና ባፍንጫው የሚወጣው ጭሱ
እናትና አባቱ እንዳንተ በጊዜ ቢያጥኑት በበርበሬ
ብርቅ አይሆንም ነበር  ለትንባሆ ዛሬ
ዛሬም ያንተን ጥጋብ ልክ ካላገባው
     የበርበሬ ጭሱ
ትንሽ ከፍ ስትል ትብሳለህ ከሱ
ቶሎ ካልተዘጋ የአመል በራፍህ
ይገባል ሲጋራ በመሀል ጣትህ
አለችና እናቴ ደግማ ወደጭሱ አንዴ
      ብትመልሰኝ
የወደፊቱን ሱስ ነቅሎ እያስነጠሰኝ
ሲጋራ እንዳላጨስ በርበሬው አጨሰኝ

2 comments:

  1. በርበሬ አጨሰኝ
    በ ቴዲ አፍሮ

    ReplyDelete
  2. Mirti Ena Lewetato Tmihrt senhce GITIM THANKYOU MY HARO

    ReplyDelete